በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱርክ ከግዛቷ እንድትወጣ ኢራቅ ጠየቀች


‘ቱርክ አድርሳዋለች’ የተባለው ጥቃት ኩርድ ግዛት ዶሁክ
‘ቱርክ አድርሳዋለች’ የተባለው ጥቃት ኩርድ ግዛት ዶሁክ

ቱርክ “ከኢራቅ ግዛት ለቅቃ እንድትወጣ እንፈልጋለን” ሲሉ የኢራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጥያቄ አቀረቡ።

ጥያቄው የቀረበው ኢራቅ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያ ሥፍራ ላይ ‘ቱርክ አድርሳዋለች’ የተባለውን ጥቃት ተከትሎ የኢራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉአድ ሁሴን ለምክር ቤቱ አባላት ትናንት ባሰሙት ንግግር ነው።

“በኢራቅ ግዛት ውስጥ የቱርክን ወታደራዊ ኃይሎች ህገወጥ እንቅስቃሴ እናወግዛለን” ብለዋል ሚኒስትሩ።

ባለፈው ሣምንት፣ ሀምሌ 13 በኩርድ ግዛት ዶሁክ ውስጥ በሚገኘው የመዝናኛ ሥፍራ ላይ በተፈፀመ ጥቃት ሦስት ህፃናትን ጨምሮ 9 ሲቪሎች መገደላቸው ተዘግቧል።

ባግዳድ አንካራን ከስሳ ካሣ የጠየቀች ሲሆን በጥቃቱ ላይ ዓለምአቀፍ ምርመራ እንዲደረግም ጠይቃለች።

ቱርክ በሚዋሰናት የኩርድ ግዛት ውስጥ ‘ፈፅመዋለች’ የተባለውን ጥቃት አስተባብላለች።

XS
SM
MD
LG