በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ ሞቃዲሹ የሆቴል ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገደሉ


ሶማሊያ ዋና ከታማ ሞቃዲሹ የሚገኘው ቤተ መንግሥት
ሶማሊያ ዋና ከታማ ሞቃዲሹ የሚገኘው ቤተ መንግሥት

በድጋሚ የታደሰ

ሶማሊያ ዋና ከታማው ሞቃዲሹ ውስጥ በፕሬዚዳንቱ ቤተመንግሥት አቅራቢያ በሚገኘው ሆቴል ውስጥ ታጣቂዎች ዛሬ እያደረሱ ባሉት ጥቃት የሶማሊያ የደህንነት ሚኒስትር እና ምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ የቆሰሉ ሲሆን ቢያንስ ሌሎች ሰባት ሰዎች ደግሞ መገደላቸውን ተሰማ፡፡

ቪላ ሬይስ በተባለው ሆቴል ላይ የደረሰው ጥቃት ሁለተኛውን ቀን ያስቆጠረ ሲሆን የጸጥታ ኃይሎች እሁድ ምሽቱን ጥቃት ማድረስ ከጀመሩት የአልሸባብ ቡድን ተዋጊዎች ጋር እየተዋጉ መሆኑ ተነገሯል፡፡

ቪላ ሬይ ሆቴል፣ ብዙ ጥበቃ ከሚደረግለት ቤተመንግሥትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን በመንግሥት ባለሥልጣናት የሚዘወትርና ወደዚህ ሥፍራ ለመድረስ የይለፍ ወረቀት የሚያስፈልግ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የሆቴሉ ጥቃት የተከሰተው የሶማሊያ ጦር በሐምሌ ወር በአሸባሪው ቡድን ላይ ዘመቻ ከጀመረ ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን የፌዴራሉ መንግሥት ባወጀበት ወቅት ነው።

በጥቅምት ወር መገባደጃ ላይ በሞቃዲሹ በደረሰ መንታ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ 100 ሰዎች ተገድለዋል። ለጥቃቱ አልሸባብ ሃላፊነቱን ወስዷል።

የጸጥታው ኃላፊ ሞሃመድ ዳሂር ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት ታጣቂው በህንጻው የሆቴሉ ክፍል ውስጥ እንዳለ የተከበበ መሆኑን ጠቅሰው “የጸጥታ ኃይሎች የጥቃቱን ድርጊቱ በቅርቡ እንዲያበቃ ያደርጉታል ማለታቸው” በዘገባው ተመልክቷል፡፡

በቴሌግራም እና ሌሎች መሰል ማኅበራዊ የመገናኛ መድረኮች ታጣቂው ቡድን ባሳፈረው ጽሁፍ፣ እግረኞቹ ተዋጊዎቹ የአጥፍቶ ጠፊ ተልዕኮአቸውን ፈጽመዋል ብሏል፡፡

ፖሊስ በርካታ ሲቪሎችንና ባለሥልጣናትን ማዳኑን የገለጸ ሲሆን፣ የዓይን እማኞችም ልዩ የጸጥታ ኃይሎች ወደ ሥፍራው ሲንቀሳቀሱ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG