ዋሺንግተን ዲሲ —
ግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ አቅራቢያ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ዛሬ ዓርብ ተኩስ የከፈተው ታጣቂ ቢያንስ አራት ሰዎች ገደለ። ሌሎች አምስት ሰዎች አቁስሏል። ከሞቱት መካከል አንዱ ፖሊስ መሆኑ ታውቋል።
ሄልዋን ወረዳ ውስጥ ቅድስት ማሪያም ሚና ኦርቶዶክስ ቤተ ክስርስቲያንድ ደጃፍ ተኩስ የከፈተው ታጣቂ ተታኩሶ መገደሉን የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ገልፀዋል።
ሁለተኛ ታጣቂ ይኖራል በሚል ጥርጣሬ ፖሊሶች ፍለጋ ላይ መሰማራታቸውን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል።
ለዛሬው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ ወገን እስካሁን የለም። ይሁን እንጂ ባለፈው ዓመት ውስጥ አብያተ ክርስቲያን ላይ በደረሱትና ብዛት ያላቸው ምዕመናን ለተገደሉባቸው ጥቃቶች እስላማዊ መንግሥት ኃላፊነት ሲወስድ ቆይቷል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ