በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቶጎ በፀጥታ ኃይሎችና ተቃዋሚ ሰልፈኞች በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተገደሉ


Map of Togo, Africa
Map of Togo, Africa

ቶጎ ውስጥ በፀጥታ ሃይሎችና የፕሬዚደንት ፎሬ ኛሲኒቤ አገዛዝ እንዲያበቃ በጠየቁ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ።

ቶጎ ውስጥ በፀጥታ ሃይሎችና የፕሬዚደንት ፎሬ ኛሲኒቤ አገዛዝ እንዲያበቃ በጠየቁ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አራት ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ።

ዛሬ የቶጎ የፀጥታ ሚኒስትር ኮሎኔል ዳሜሄሚ ያርክ በሰጡት መግለጫ ዋና ከተማዋ ሎሜ ውስጥ አንድ ሰው ሦስት ሰዎች ደግሞ ሁለተኛ ትልቁዋ ከተማ በሆነችው ሶዶኬ ውስጥ መገደላቸውን ገልፀዋል።

ከትናንቱ ግጭት በተያያዘ ስልሳ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መታሰራቸውንም ባለሥልጣኑ ጨምረው አስረድተዋል።

ተቃዋሚ መሪዎች እኤአ ከ2005 አባታቸው ኛሲኒቤ ኢያዴማ ካረፉ በኋላ ሥልጣን የጨበጡትን ያሁኑን መሪ በመቃወም የሁለት ቀን የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

የአሁኑ ፕሬዚደንት በህገ መንግሥቱ የተደነገገው ፕሬዚደንታዊ የሥልጣን ዘመን ገደብ እንዲሰረዝ ያቀረቡትን ሃሳብ በመቃወም በሀገሪቱ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀስቅሰዋል።

ፕሬዚደንቱ ያቀረቡት ሃሳብ ከተሳካላቸው ቢያንስ እአአ 2030፣ ለቀጣዮቹ አሥራ ሁለት ዓመት መንበረ ሥልጣኑ ላይ ተደላድለው ለመቀመጥ ይመቻቸዋል። አባትየውም ቢሆኑ ከ1968 እስካረፉበት 2005 ዓመተ ምህረት ድረስ ሥልጣን ላይ ቆይተው ነው ለልጃቸው አምቻችተው ያለፉት፣ ሰላሳ ሰባት ዓመት ገዝተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG