ዋሽንግተን ዲሲ —
በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምስራቃዊ የአገሪቱ ክፍል በሚገኘው የተፈናቃይ ሰዎች መጠለያ ካምፕ ላይ በተሰነዘረ የሚሊሺያዎች ጥቃት ቢያንስ 60 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ፡፡
የአካባቢው የረድኤት ድርጅቶችና የዐይን እማኞች እንደገለጹት ለግድያው ኃላፊነቱን የወሰዱት ከሊንዱ ማህበረሰብ የወጡ የገበሬዎች ሚሊሻ ቡድኖች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
ተባበሩት መንግሥታት እንዳመለከተው እስካለፈው ታህሳስ ወር ድረስ በመጠለያ ካምፑ 4ሺ ተፈናቃዮች ይኖሩበታል፡፡