በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ ውስጥ ሃምሳ ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ


ከኒዠር ጋር በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ማዕከላዊ ማሊ የሚገኙ ሦስት መንደሮችን ታጣቂ እስላማዊ ቡድን አባላት ትናንት በአንድ ጊዜ ወርረው ጥቃት እንዳደረሰ የወረዳው አስተዳዳሪ ገልጸዋል።

ብዙዎች መቁሰላቸውን እና ንብረት መዘረፉን እና መቃጠሉን ባለሥልጣኑ አክለዋል። ለጥቃቱ ኃላፊ ነኝ ያለ ወገን እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት አካባቢ የማሊ ወታደሮች እና የፈረንሳይ እንዲሁም የተመድ የሠላም አስከባሪዎች ከታጣቂዎች ጋር የሚዋጉበት ነው።

XS
SM
MD
LG