በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካቡል ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ አርባ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ ትናንት በአንድ የመንግሥት ሕንፃ ላይ ጥቃት የከፈቱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው አርባ ሦስት ሰው መግደላቸው ተዘግቧል።

አፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ ትናንት በአንድ የመንግሥት ሕንፃ ላይ ጥቃት የከፈቱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው አርባ ሦስት ሰው መግደላቸው ተዘግቧል።

ከቀትር በኋላ ተጀመረ በተባለው ጥቃት አንድ አጥፍቶ ጠፊ ወደ ሕንፃው ዘልቆ የታጠቀውን ፈንጂ ካፈነዳ በኋላ ውጭ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ውስጥ ታጭቆ የነበረ ፈንጂ ብዙ የመንግሥት ተቋማት በሚገኙበት በዚሁ ሕንፃ ላይ ብርቱ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል።

በፍንዳታዎቹ ምክንያት ወደ ተከፈተው የሕንፃው መግቢያ ፈጥነው የገቡ ታጣቂዎች ከፖሊስ ጋር ግብግብ ገጥመው ለሰባት ሰዓታት የቆየ ተኩስ መለዋወጣቸው ተገልጿል።

በየመሥሪያ ቤቱ ይሠሩ የነበሩ 200 ሰዎች ያለጉዳት እንዲወጡ መደረጉን ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG