በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን ውስጥ በሩሲያ የሚሳይል ጥቃት ቢያንስ 35 ሰዎች ተገደሉ


ሩሲያ ዲኒፕሮ በተባለች የዩክሬን ከተማ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ያደረሰችው የሚሳይል ጥቃት
ሩሲያ ዲኒፕሮ በተባለች የዩክሬን ከተማ የመኖሪያ ህንጻ ላይ ያደረሰችው የሚሳይል ጥቃት

ሩሲያ ዲኒፕሮ በተባለች የዩክሬን ከተማ በመኖሪያ ህንጻ ላይ ባደረሰችው የሚሳይል ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 35 መድረሱን የዩክሬን ባለሥልጣናት ተናገሩ።

በጥቃቱ 75 ሰዎች መቁሰላቸውን የገለጹት የዲኒፕሮ ክፍለ ግዛት ባለሥልጣናት በህይወት የተረፉ ሰዎች ይኖሩ እንደሆን ፍለጋው መቀጠሉን ገልጸዋል።

ከሞቱት እና ከቆሰሉት ሌላ ያልተገኙ ከ35 የሚበልጡ ሰዎች መኖራቸውን ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል።

የሚሳይል ጥቃቱ የደረሰው ቅዳሜ መሆኑን የዩክሬን የአየር ኃይል አስታውቋል። ሩሲያ ተመሳሳይ ውንጀላዎችን በተደጋጋሚ ስታትስተባብል ቆይታለች።

ዛሬም የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስትር ዲሚትሪ ፔስኮቭ ኃይሎቻችን ወታደራዊ ዒላማዎች እንጂ የሲቪሎች መኖሪያ ህንጻዎችንም ሲቪላዊ መሰረተ ልማቶችን ኢላማ አያደርጉም በማለት አስተባብለዋል።

ዲኖፒሮ ላይ ጥቃቱን ያደረሱት የዩክሬን የአየር መከላከያ ኃይሎች ናቸው ማለታቸውም ተጠቅሷል።

ይህ በዚህ እንዳለ የዩክሬን ሰሜናዊ አጎራባች የሆነችው ቤላሩስ በዛሬው ዕለት ከሩሲያ ጋር የጋራ ወታደራዊ ልምምድ መጀመሯ ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG