በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞች ጀልባ ላይ በደረሰ ቃጠሎ የሰው ህይወት አለፈ


የጣሊያን የአዮኒያ ባህር ጠረፍ ላይ ፍልሰተኞች ያሳፈረ ጀልባ ላይ በደረሰ ቃጠሎ ሦስቱ መሞታቸው አንድ በቃጠሎው መጎዳቱ የሃገሪቱ ፖሊሶች ተናገሩ። የደረሰበት የጠፋ ስደተኛ መኖሩንም አመልክተዋል።

ፖሊሶች እንዳሉት ቃጠሎው የተነሳው ጀልባዋ ሞተር ላይ ነው፤ ምን ያህል ተሳፋሪዎች እንደነበሩ ለጊዜው አልታወቀም ብለዋል፤ ይሁን እንጂ በዘገባዎች መሰረት ሃያ አንድ ፍልሰተኞች ነበሩ። ፖሊሶች ከቃጠሎው በፊት አሥራ ሦስቱን አጅበው አውርደዋቸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጣሊያንን መሬት የሚረግጡ ፍልሰተኞችን የሚበዙትን የምትቀበለዋ የላምፔዱሳ ደሴት ነዋሪዎች በቅርብ ጊዜያት የሚገቡ ፍልሰተኞች በመብዛታቸው ከመንግሥት ተጨማሪ እርዳታ በመጠየቅ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተዘግቧል።

ትናንት እሁድ ሌሊት አንድ ያረጀ የአሳ አጥማጅ ጀልባ ያሳፈራቸው አራት መቶ ሃምሳ ፍልሰተኞች ደሴቲቱ ላይ ማወረዱን ተከትሎ የላምፔዱሳ ከንቲባ ህዝቡ ከመንግሥት ተጨማሪ ድጋፍ እንዲሰጥ አጠቃላይ የሥራ ማቆም አድማ እንዲመታ ጥሪ አድርገዋል።

የጣሊያን መንግሥት ይህንኑ ተከትሎ ለለይቶ ማቆያነት የሚውሉ ሦሶት ጀልባዎችን ልኳል። እስከ ዕረቡ ደግሞ ሁለት ተጨማሪ ጀልባዎች እንልካለን ብሏል።

XS
SM
MD
LG