በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ ጎርፍ 21 ሰው ገደለ


ሶማሊያ ውስጥ የደረሰ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ስድስት ሕፃናትን ጨምሮ የ21 ሰው ሕይወት መቅጠፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) አስታወቀ።

ወትሮውንም በድርቅ በተጠቃው የደቡብ ሶማሊያ ጌዶ ክልል፣ ከባድ ዶፍና ጎርፍ ባስከተለው አደጋ 100 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ችግር ላይ መጣሉን ኦቻ አስታውቋል።

በጎርፍ የተጠቃው አካባባቢ በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ በመኾኑ የሸበሌ እና የጁባ ወንዞች የውሃ መጠን ከፍ ብሏል፡፡

የሶማሊያ ብሔራዊ አደጋ መከላከያ ቢሮ በበኩሉ የጤና ማዕከላት በጎርፉ መውደማቸውን አስታውቋል፡፡ የቢሮው አማካሪ ሞሃመድ ሞአሊም ለአሶስዬትድ ፕረስ እንደተናገሩት በወንዞች አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች አደጋ ላይ እንደሆኑ እንዲያውቁት ተደርጓል፡፡

አራት ትምህርት ቤቶችና 200 መጸዳጃ ቤትች በጎርፉ መፍረሳቸው ታውቋል፡፡ በዚህም መክንያት የ3000 ሕጻናት ትምህርት መስተጓጎሉን እና ከ1ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት በጎርፍ መታጠቡንም ኦቻ ጨምሮ አስታውቋል፡፡

የጎርፍ አደጋው የመጣው አገሪቱ እየቀጠለ ባለው ድርቅ ምክንያት 8.25 ሚሊዮን ሠዎች የሰብዓዊ ርዳታ ጠባቂ እንዲሆኑ ባደርገበት ወቅት ነው፡፡ 1.4 ሚሊዮን ሰዎች በድርቁ ምክንያት መፈናቀላቸውም ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG