ዋሺንግተን ዲሲ —
ኒዠር ውስጥ በዋና ከተማዋ ኒያሜ በሚገኝ ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸው ሰዎች መኖሪያ ቀበሌ በሚገኝ ትምህርት ቤት መዋዕለ ህፃናት ትናንት ቃጠሎ ደርሶ ቢያንስ ሃያ ህፃናት መሞታቸው ተገለጸ።
ትምህርት ቤቱ ስምንት መቶ ተማሪዎች የሚማሩበት ሲሆን መግቢያው በር ላይ የተቀሰቀሰው ቃጠሎ በምን ምክንያት እንደተነሳ ገና ግልፅ አለመሆኑን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቱ የአደጋ ጊዜ ማምለጫ በር የሌለው በመሆኑ አብዛኞቹ ህፃናት መውጫ ማጣታቸውን የእሳት አደጋ አገልግሎት ባለሥልጣናት ጨመረው ገልፀዋል።