በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን በአውሮፕላን አደጋ የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን ጨምሮ 15 ሰዎች ሞቱ


የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቪ አቅራቢያ በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር አደጋ የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን ጨምሮ ቢያንስ አስራ አምስት ሰዎች ሞቱ።
የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቪ አቅራቢያ በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር አደጋ የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን ጨምሮ ቢያንስ አስራ አምስት ሰዎች ሞቱ።

የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቪ አቅራቢያ በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር አደጋ የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩን ጨምሮ ቢያንስ አስራ አምስት ሰዎች ሞቱ።

ሄሊኮፕተሩ የወደቀው ከአንድ የህጻናት ትምህርት ቤት አቅራቢያ ሲሆን ከሞቱት ሰዎች መካከል ዘጠኙ ተሳፋሪዎች መሆናቸው ተገልጿል። የአደጋው ምክንያት ለጊዜው በግልጽ አልታወቀም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በ2023 ሩሲያ ዩክሬን ላይ የምታካሂደው ጦርነት በአጭር ጊዜ ይቆማል ብለው እንደማይጠብቁ ተናገሩ። ጉቴሬዥ ይህን ያሉት ስዊዘርላንድ ዳቮስ ላይ በመካሄድ ላይ ያለው የዓለም ኢኮኖሚ ጉባዔ ፕሬዚዳንት ቦርገ ብረንድ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ነው።

"ባሁኑ ሰዓት በሁለቱ ወገኖች መካከል ጠንካራ የሰላም ድርድር የሚደረግበት ዕድል አይታየኝም " ብለዋል ዋና ጸኃፊው።

በተያያዘ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎችም የዩክሬን አጋሮች የተራቁቁ የጦር መሳሪያዎች እና ስልጠና በመስጠት ላይ ሲሆኑ የፊታችን አርብ በጀርመን የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ኃይል በሚከፈተው አሜሪካ መራሽ በሚከፈተው የዩክሬን መከላከያ ድጋፍ ስብሰባ ላይ ተጨማሪ እርዳታ ሳይደረግ እንደማይቀር ተመልክቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስተን በሚመሩት ስብሰባ ላይ በርካታ የመከላከያ ሚንስትሮች ይሳተፋሉ። የኔቶ ዋና ጸሐፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ እና የዩክሬን የመከላከያ ሚንስትር ኦሊክሲ ሬዝኒኮቭም እንደሚገኙ ታውቋል።

ጀርመን እና ዩናይትድ ስቴትስ ፓትሪዮት የሚባለውን ተሽከርካሪ ከየብስ ወደሰማይ ተተኳሽ ሚሳይል እና ተወንጫፊ ሚሳይል አውራጅ ሊለግሱ ቃል ገብተዋል። ለዩክሬን ኃይሎች ሥልጠና መስጠት መጀመሩን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG