በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያው ጥቃት ቢያንስ 140 ሰዎች ተገደሉ


ፎቶ ፋይል፦ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ
ፎቶ ፋይል፦ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ

በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ ፕላቱ ክፍለግዛት ባላፈው ቅዳሜ አጥቂዎች ዒላማ ባደረጓቸው 17 የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ባደረሱት ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የክፍለ ግዛቱ አገር ገዥ ተናገሩ፡፡

አገረ ገዥው ካሌብ ሙትፍዋንግ ዛሬ ማክሰኞ ለአገር ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያ ማንጉ በተባለው አካባቢ 15 የሚደርሱ አስክሬኖችን እየቀበሩ መሆኑን ገልጸው፣ ቦኮስ በተባለው አካባቢ እስከዛሬ ጧት ድረስ ከመቶዎች ያላነሱ አስክሬኖችን እየቆጠርን ነው” ብለዋል፡፡

ባርኪን ላዲ በተባለው አካባቢ በርካታ ሟቾች እንደሚኖሩ የገለጹት አገረገዥው “እዚህ ፕላቱ ግዛት ውስጥ ለኛ እጅግ አስፈሪ የሆነ የገና በዓል ነበር” ብለዋል፡፡

ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን የለም፡፡ ይሁን እንጂ በአካባቢው በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መካከል ውጥረት መኖሩ በዘገባው ተመልክቷል፡፡

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የናይጄሪያ ፅህፈት ቤት ለአሶሼትድ ፕሬስ እንደገለጸው፣ ክርስቲያኖች በሚበዙባቸው የቦኮስ እና ባርኪን ላዲ አካባቢዎች ከ140 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለሥልጣኖች አረጋግጠዋል፡፡

የሟቾች ቁጥር ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል የተገለጠ ሲሆን የተወሰኑ ሰዎች እስካሁ የደረሱበት አልታወቀም።

የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ቃል የገቡት የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግሥት የሰጠውን ምላሽ በቂ አለመሆኑን በመጥቀስ የዜጎችን ደህንነት በመጠበቅም ሆነ ለተጎጂዎች ፍትህ በመስጠት ደካማ ነው መሆኑን ተችቷል፡፡

የናይጄሪያ ጦር አጥቂዎቹን ለማግኘት እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን የጦሩ አዛዥ አብዱልሰላም አቡበከር ወንጀለኞቹን ለፍርድ ለማቅረብ ቃል ገብተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG