በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቃዲሾ በፈንጂዎች የተሞላ መኪና ፈንድቶ 14 ሰዎች ተገድለዋል


በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ዛሬ በፈንጂዎች የተሞላ መኪና ፈንድቶ ቢያንስ 14 ሰዎች ተገድለዋል።

በሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ዛሬ በፈንጂዎች የተሞላ መኪና ፈንድቶ ቢያንስ 14 ሰዎች ተገድለዋል።

የሶማልያ ባለስልጣኖች በተናገሩት መሰረት መኪናው የፈነዳው ፖለቲከኞችና ነጋዴዎች በሚያዘወትሩበት ዊሀሊይ በተባለው ሆቴል ውጭ ነው። ሆቴሉ የሚገኘው ማካ አል ሙካራማ በተባለው ሰዎች የሚበዙበት መንገድ ላይ ነው።

“ከሆቴሉ ውጭ ሰው በሚበዛበት መንገድ ላይ ቆሞ የነበረ በፈንጂዎች የተሞላ መኪና ፈንድቶ 14 ሰዎች መሞታቸውንና አምስት መቁሰላቸውን አረጋግጠናል” ሲሉ የፀጥታ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አብደል አዚዝ ሒልዲሂባን ተናግረዋል።

የጥቅቱ ዓላማ ምን እንደሆነ እስካሁን ባለው ጊዜ ግልፅ አለመሆኑን የመንግሥት ባለሥልጣኖች ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG