ዋሺንግተን ዲሲ —
በሕክምናው የእንግሊዝኛ አጠራር Post Traumatic Stress Disorder በመባል በሚታወቀው የአእምሮ ሁከት ዙሪያ ትኩረት የሚያደርግ ዝግጅት ነው።
እጅግ የከፋ አደጋ ያስከተለ ድንገትን ተከትሎ የሚመጣ የአንጎል ሕመም ምንነትና ሕክምና የሚያብራሩልን ፕሮፌሰር መስፍን አረአያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአምሮ ሕክምና መምሕርና አማካሪ ሃኪም ናቸው።
በኢትዮጵያ በቅርቡ በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱት አሰቃቂ ድርጊቶችና ከበርካታ ዓመታት በፊት በዘመነ አብዮት የተፈጸሙ ለዚህ መሰል የአእምሮ ሁከት ሊያጋልጡ የሚችሉ ዘግናኝ ሁኔታዎች በማዛመድ ይመረምራሉ።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ