በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመዘንጋት ችግር በወጣትነት ዕድሜ ክልል ሲከሰት?!


በወጣትነት የመዘንጋት አዝማሚያ በብዛት የሚከሰተው፥ በአመዛኙ በኑሮ ጫናና በውጥረት ነው። የአልኮል አዘውታሪነት፤ ከልክ በላይ ለረዥም ጊዜ አልኮል መጠጣት፤ ከሰዎች ጋር የመጋጨት፤ ትንሹን ትልቁን የሚያመርና ይቅር የማይል ባህሪ ባለቤትነት፤ አንዳንድ መድሃኒቶችና አንዳንድ ተላላፊ በሽታዎች ከመርሳት በሽታ ጋር ሊያያዙ ይችላሉ።

የመዘንጋት ችግር በወጣትነትና በጎልማሳነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሠዎች ላይ ሲከሰት ያለውን ሁኔታ፥ ምንነትና፤ ተዛምደው ሊታዩ የሚገቡ ዝርዝሮች፤ እንዲሁም ችግሮቹን ለማቅለል የሚረዱ ዕርምጃዎች ጨምሮ ለማየት የሚሞክር ቅንብር ነው።

በእነዚህ በመርሳት ችግሮች ዙሪያ ላተኮሩት ነጥቦች ሞያዊ ትንታኔ የሚሰጡን፥ ዛሬም የአዕምሮና የነርቭ ህክምና ባለሞያው፥ ዶ/ር ዮናስ እንዳለ ገዳ ናቸው።

ዶ/ር ዮናስ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የታዋቂው ሜዮ ክሊኒክ፥ የህክምና ኮሌጅ የአዕምሮና የሥነ ልቦና ትምህርት ክፍል ምክትል ሊቀመንበርም ናቸው።

ለዝርዝሩ ከዶ/ር ዮናስ ጋር የተካሄደውን የመጨረሻ ክፍል ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG