በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጀርመኑ ቀኝ አክራሪ ፓርቲ ድጋፍ ማሰባሰቡን ቀጥሏል


ፎቶ ፋይል፦ የቀኝ አክራሪው 'አማራጭ ለጀርመን' ፓርቲ ደጋፊዎች የጀርመን ብሔራዊ ባንዲራ ይዘው ለመጪው የክልል ምርጫ ፓርቲው በሚያደርገው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ በሱህል፣ ጀርመን
ፎቶ ፋይል፦ የቀኝ አክራሪው 'አማራጭ ለጀርመን' ፓርቲ ደጋፊዎች የጀርመን ብሔራዊ ባንዲራ ይዘው ለመጪው የክልል ምርጫ ፓርቲው በሚያደርገው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ በሱህል፣ ጀርመን

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2013 የተመሰረተው የቀኝ አክራሪው 'አማራጭ ለጀርመን' ፓርቲ በመላ ሀገሪቱ ጠንካራ ድጋፍ እያገኘ መኾኑ ተገልጿል። ጀርመን በዚህ ወር ለምታካሂደው አጠቃላይ ምርጫ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ፓርቲ የሚያገኘው ድጋፍ የጨመረው፣ በዋናነት በሀገሪቱ በሚገኙ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ምክንያት መሆኑም ተመልክቷል።

የስደተኞች ጉዳይ፣ ፓርቲው ማዕከል አድርጎ የሚሠራበት ዋና አጀንዳ ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሩሲያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በአስቸኳይ ማንሳትን የመሳሰሉ ሌሎች ጉዳዮች ላይም ትኩረት ማድረግ ጀምሯል።

አፍዲ በሚል ምጽሃረ ቃል የሚጠራው አማራጭ ለጀርመን ፓርቲው ለቻንስለርነት እንዲወዳድሩ ያጫቸው አሊስ ዊዴል፣ ስደተኞችን በጅምላ ወደመጡበት መመለስ የሚለው አዲስ ፅንሰ ሐሳብ ደጋፊ መሆናቸው ተመልክቷል።

የፖለቲካ ተንታኞች ዊዴል ቻንስለር የመሆን እድላቸው አናሳ ነው ቢሉም፣ የፓርቲው ድጋፍ እየጨመረ መሄድ፣ ፖለቲከኞች በስደተኞች ዙሪያ የሚያደርጓቸውን ውይይቶች እና ክርክሮች እንደገና እንዲያስቡበት እያስገደዳቸው ነው።

አፍዲ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ መቀመጫ ያገኘው እ.አ.አ በ2017 ዓ.ም 12.6 ከመቶ ድምፅ አግኝቶ ነው። ፓርቲው የፖለቲካ ተዋናይ ሆኖ ድጋፍ እያገኘ ባለበት ወቅትም፣ የኦስትሪያው ፍሪደም ፓርቲ እና የፈረንሳዩ ናሽናል ራሊ የመሳሰሉ ቀኝ አክራሪ ፓርቲዎች ያላቸው ተቀባይነት እያደገ መሆኑ ተመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG