በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቢጨምሩም ሆስፒታል ገቢዎች አነስተኛ ናቸው


ፎቶ ፋይል፦ የጤና ባለሞያው ሰዎች ከመኪናቸው ሳይወርዱ ለኮቪድ መጋለጥ፣ አለመጋላጣቸውን ምርመራ ሲደርግላቸው እአአ ዲሴምበር 29/2021ሚያሚ
ፎቶ ፋይል፦ የጤና ባለሞያው ሰዎች ከመኪናቸው ሳይወርዱ ለኮቪድ መጋለጥ፣ አለመጋላጣቸውን ምርመራ ሲደርግላቸው እአአ ዲሴምበር 29/2021ሚያሚ

ዩናይትድስ ስቴትስ ውስጥ የኦሚክሮን ቫይረስ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ ቢሆንም ወደ ሆስፒታል የሚገቡና በቫይረሱ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በአንጻራዊነት ሲታይ ዝቅተኛ መሆኑን ሲዲሲ ትናንት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች ቁጥጥና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) ድሬክተር ሮሼል ዎልንስኪ ትናንት በዋይት ሀውስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫቸው ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎች ከእስከዛሬዎቹ ከፍተኛውን ደረጃ መያዙን ገልጸዋል፡፡

ድሬክተሯ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ኦሚክሮን በመላ አገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋቱን የገለጹ ሲሆን በተከታታይ ሳምንታትም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የሲዲሲ ድሬክተር በመግለጫቸው አሁን ያለው ተጋላጭነት ካለፈው ሳምንት በ60 ከመቶ የጨመረ መሆኑን ገልጸው በየቀኑ 240 400ሺ ሰው የሚጋለጥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በየቀኑ 9ሺ000 ሰዎች ወደ ሆስፒታል የሚገቡ መሆኑን ገልጸው ቁጥሩ በ14 ከመቶ ያደገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በቀን 1ሺ000 ሰዎች ሲሆን በፊት ከነበረው በ7 ከመቶ መቀነሱን አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG