በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣትና የተደራዳሪዎች አመለካከት


የብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣትን አስማልክቶ የሀገሪቱና የአውሮፓ ህብረት ተደራዳሪዎች ዛሬ የተለያየ አመለካከት አንፀባርቀዋል።

የብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣትን አስማልክቶ የሀገሪቱና የአውሮፓ ህብረት ተደራዳሪዎች ዛሬ የተለያየ አመለካከት አንፀባርቀዋል። የብሪታንያ የምክር ቤት አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ መይ፣ የአወጣጡን ሥምምነት በሚመለከት ለውጥ እንዲደረግ እንዲጠይቁ የብሪታንያ የምክር ቤት አባላት “ውክልና” ሰጥተውኛል ካሉ በኋላ ነው ልዩነቶቹ የተሰሙት።

ትላንት በብሪታንያ ምክር ቤት በተሰጡት ተከታታይ ድምፆች የብሪታንያን አወጣጥ አስመልክቶ በተደርገው ሥምምነት መይ ለአየርላንድ የድንበር ውሳኔ አማራጭ ቅንጅቶች እንዲደረጉ በሚያስችል ሁኔታ ለመዳራደር ያላቸው እቅድ ይሁንታ አግኝቷል።

የብሪታንያን ከአውሮፓ ህብረተ መወጣት ጉዳይ ዋናው የአውሮፓ ህብረት ተደራዳሪ ሚካኤክ ባርኔር አቋማችን ግልፅ ነው ብለዋል። ግልጽ ለማድረግ የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው። ከብሪታንያ ጋር በተደራደርነው ሥምምነት በመጽናት ረገድ በአንድነት እንቆማለን ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG