በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት ጥበበኛ እጆች


ተወልዶ ያደገው ናዝሬት ከተማ ነው። አብዱረዛቅ ረሽድ አደም ገና በስምንት ዓመቱ የሰርከስ ልምምድ ለማድረግ ከትምህርት ቤት መልስ ከበጎ ፈቃድ አሰልጣኙ ሙያ ሊቀስም ሲሄድ ቤተሰቦቹ ደስተኞች አልነበሩም።

“ይሄንን ቧልትና ዝላይ ትተህ በትምህርትህ በርታ” ነበር የወላጆቹ ምክር። በየቀኑ ወሳኝ ክህሎቶቹን እየተማረ የነበረው አብዲ ግን ተደብቆም ቢሆን ከልምምድ አይቀርም ነበር።

“ቤተሰቦቼ ጊዜየን የከንቱ የማሳልፍ ይመስላቸው ነበር” ይላል አብዲ። የኋላ ኋላ ቤተሰቦቹን ከትርዒቶቹ አንዱን እንዲመለከቱለት ጋብዟቸው ስራውን ካዩ በኋላ ድጋፋቸውን ሰጡት።

ዛሬ ይሄ ታዳጊ ወጣት የ27 ዓመት ሰው ነው። በስራውም ቢሆን በልጅነቱ ያደረበትን የሰርከስ ፍቅር ወደ ፕሮፌሽናል ሙያ ቀይሮት ታዋቂ ሆኗል።

ሲጀምር ሰርከስ ናዝሬት ፥ ከዚያ ሰርከስ ኢትዮጲያ ፥ ዛሬ ደግሞ በዓለም ላይ የታወቀ ባውንሲንግ ጀግለር ወይም በርካታ ኩዋሶችን በማንጠር በቅንብር እየቀለበ በታላላቅ የዝናኛ ማዕከላት እና በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ከተሞች ስራውን ያቀርባል።

ለሰርከስ ትርኢቱ ወዲህ ወደዩናይትድ ስቴትስ መጥቶ በዋሽግተን ዲሲ እና በተለያዩ በርካታ ከተሞች እየተዘዋወረ ነው። በታወቀው በኬኔዲ ሴንተር ዝግጅቱን ከአውሮፓ ከተሰባሰብ የሰርከስ ቡድን ጋር አቅርቧል በሌሎችም ከተሞች እንዲሁ እየተዘዋወረ ዝግጅቶቹን ያቀርባል። ከመስታዎት ዝግጅት ጋር ያደረገውን ሙሉ ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG