ሰሞኑን በዩቱብ በተሰራጨው የቴሌቭዥን ዜና አሠሪዋ ቤሩት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ደጃፍ በአሰቃቂ ሁኔታ እያንገላታና በግድ እየጎተተ ወደ መኪና ሲያስገባት የታየቸው ዓለም ደቻሳ በትላንትናው ዕለት ሕይወቷ ማለፉ ታወቋል።
የቆንስላ ቢሮው ተጠሪ አቶ አሳምነው ደበሌ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጡት፥ የሦስት ልጆች እናት የሆነቸው ዓለም ለህክምና ተወስዳ በነበረበት ሆስፒታል ሌሊቱን ራሷን ሰቅላ ተገኝታለች ብለዋል።
በቤሩት ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ልጅቱን ከአሠሪዋ ጥቃት ሊስጥላት በተገባ ነበር በማለት ቁጣ ማሰማታቸውን ያካተተውን የዚህን ዘገባ ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ።