በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ መንግስት ባለሥልጣናት ከእስር ተፈቱ


ቀደም ሲል የተፈረደባቸዉ የሞት ቅጣት፣ ከተሻሻለላቸዉ ከፍተኛ የቀድሞ ባለስልጣናት መካከል አስራ ስድስቱ ከሃያ ዓመታት እስር በኋላ በትናንትናዉ እለት ተፈተዋል።

በሞት እንዲቀጡ ከተወሰነባቸዉ መካከል፣ ሃያ ሶስቱ በዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት ናቸዉ። ጉዳዩ በይቅርታና እርቅ እንዲጨረስ፣ 4 የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት በጋራ ባደረጉት ጥረት መነሻነት የቅጣት ማሻሻያ መደረጉ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ነው ከግንቦት 20 ቀን 2003ዓም ጀምሮ የሞቱ ቅጣት ወደ እድሜ ልክ ዝቅ የተደረገዉ።

የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ምንጮችና የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች እንዳሉት፣ አስራ ስድስቱ የተፈቱት ማረሚያ ቤቱ ለፍርድ ቤት ባቀረበዉ የአመክሮ ጥያቄ መሰረት ነዉ።

በትላንትናዉ እለት ከእስር ከተፈቱት የቀድሞ ባለስልጣናት መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ፍሰሃ ደስታና ሻምበል ለገሰ አስፋዉ ይገኙበታል።

ዝርዝሩን ከዘገባው ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG