በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በFreedom House ዓመታዊ ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ ሲቃኝ!


ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት Freedom House ኢትዮጵያ በፖለቲካና ሲቪል መብት አያያዟ «ከፊል ነጻ፤» ከሚለዉ፥ «ሙሉ በሙሉ ነጻ ያልሆነች፤» ወደሚለዉ ክፍል አሽቆልቁላለች አለ።

እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ2010 በኢትዮጵያ የፖለቲካ መብትና እና የግለሰብ ነጻነት በእጅጉ የተሸረሸረበት ለመሆኑ የግንቦቱ ብሔራዊ ምርጫ ማሳያ ነዉ፤» ሲል Freedom House አመለከቷል።

«በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስተዳደር ስር ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከዴሞክራሲ እያፈገፈገች የሄደች ቢሆንም፤ ባለፉት ዓመታት ”ከፊል ነጻ” ሚለዉ የአገሮች ድልድል ዉስጥ ነበረች። በዚህ ባለፈዉ ዓመት ግን በዋናነት፥ ባለፈዉ ግንቦት ብሔራዊ ምርጫ ምክንያት፣ ”ነጻ ያልሆነች አገር” ከሚለው ድልድል ዉስጥ ገብታለች፤» ይላሉ የFreedom House ጥናትና ምርምር ኃላፊ።

ኃላፊው Arch Puddington ሲያብራሩም፤ «ከ547 የአገሪቱ ምክር ቤት መቀመጫዎች ገዢዉ ፓርቲና አጋዥ ድርጅቶቹ 545ቱን አሸነፍን ብለዋል። ለምርጫዉ የተደረገዉን ዝግጅትና የድምጽ አሰጣጡን የተከታተሉ ነጻ ታዛቢዎች ደግሞ፥ ምርጫዉ ”ዉድድር ያልታየበትና ነጻ እንዳልሆነ፣ ይልቁንም የተጭበረበረ መሆኑን ተናግረዋል፤» ብለዋል። በተጨማሪም፣ አመራሩ በዜና አዉታሮች ላይ ያለዉ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር፣ በጣም ብዙ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰራተኞችና ደጋፊዎች መታሰር፣ እነዚህ ሁሉ ኢትዮጵያ ከፍትሃዊ አስተዳደር ወደ ተቃራኒዉ አቅጣጫ እየገሰገስች መሆኑን አመልካቾች ናቸዉ፤ ብለዋል የFreedom House ጥናትና ምርምር ሃላፊው Mr. Puddington

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ካሁን ቀደም በሌሎች የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች የሚሰነዘሩባቸዉን ክሶች «እዉነትን መሰረት ያደረገ አይደለም፤» በሚል ሲከላከሉ ቆይተዋል። የወቅቱ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ፥ ባለፈዉ ግንቦት ወር የገዢዉ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሳሉ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል «ምእራባዉያን መንግስታት፣ የሊብራል የዴሞክራሲ መርሆችን እንድነቀበል ነዉ የሚገፋፉን። ለዚህ ነዉ ሁሉም የሚጣሉንና፥ የሚተቹን። ኢትዮጵያ ላከናወነችዉ ሁሉ ዋጋ መስጠት የማይፈልጉት፤» ማለታቸዉ ይታወሳል። ፓርቲያቸዉ የሚከተለዉ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ አቅጣጫ የቻይናን የኢኮኖሚ እድገት ተኮር ሞዴል የተከተለና ኢትዮጵያን ከድህነት የሚያወጣ ነዉ፤ ብለዋል።

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG