በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወ/ሪት ብርቱካን «ይቅርታ፥» እና እስር አንድምታ!


ሁለት ዓመታት ከተቃረበ እስር በኋላ በቅርቡ የተለቀቁት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወ/ሪት ብርቱካን «ይቅርታ፥» ከእስር የተለቀቁበት ሁኔታና እስር እያነጋገረ ነው።

ለመሆኑ የወ/ሪት ብርቱካን ከእስር መለቀቅ፥ አፈታታቸውና «ይቅርታው» በቀጣዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሂደት ላይ ምን አንድምታ ይኖረው ይሆን? ምንስ ዓይነት አቀባበልና ትርጓሜ ተሰጠው?

የአንድነቷን መሪ መፈታት ተከትሎ በየበኩላቸው የፃፏቸውን የቅርብ ጊዜያት ፅሁፎች ጨምሮ፤ በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በሥፋት የፃፉ አንድ የፖለቲካ ሳይንስና የህግ ምሁር፥ አንድ ጋዜጠኛ፥ እንዲሁም «ወ/ሪት ብርቱካን ነፃ ይለቀቁ፤» ወይም በእንግሊዝኛው “Free Birtukan” በሚል መጠሪያ በተለያዩ አገሮችና ልዩ-ልዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች ሲያደርግ በቆየው እንቅስቃሴ የሚታወቀው ቡድን አባል የሆነች ወጣት ጋብዘን አነጋግረናል።

ሦሥቱን እንግዶች ያነጋገረው አሉላ ከበደ ነው። የመጀመሪያውን ክፍል እነሆ፤

XS
SM
MD
LG