በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሳውዲ 35 ኢትዮጵያውያን ያለግባብ ታሰርን ይላሉ


በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ፥ ይልቁንም የኢትዮጵያውያን ዕጣ ዛሬም እያነጋገረ ነው። የሳውዲው እስር ቤት ውሎና አዳር እጅግ የከፋ መሆኑን ታሳሪዎቹ ይናገራሉ።

ለወራት የዘለቀው ቀውስ መገለል የበዛበትን የስደት ኑሯቸውን ምስቅልቅሉን ካወጣባቸው በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፥ የአምባገነኑ የሊቢያ መሪ ሞዓመር ጋዳፊ ከስልጣን መወገድ ሌላ ትርምስና ዋስትና የለሽ ህይወት እንጅ ሰላም ያላመጣላቸው በዚያች አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ዕጣ አሁንም አሳሳቢ ነው።

በተለያዩ ወገኖች በተደረጉ ጥረቶች አልፎ አልፎም በምሳሌነት ሊወሰዱ የሚችሉ ውጤቶች ቢያስገኙም ዛሬም ስቃይና እንግልት፥ ሌላ አሳዛኝ ድምጽ መሰማቱ አልቀረም።

በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ፥ ሥራ ተቀጥረው በህጋዊ መንገድ ወዲዚያች አገር የገቡ ኢትዮጵያውያን የእስር ቤት ውሎና አዳር።

XS
SM
MD
LG