የ1967ቱን አብዮትና የተከተሉትን ሁኔታዎች ጨምሮ በኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ግዙፍ ታሪክ የሚመለከት ታሪክ ቀመስ ልብወለድ ነው፤ ምርኮኛ።
በዚህ ከመፅሃፉ ጋር በምንተዋወቅበት የመጀመሪያ ክፍል ዝግጅት፥ በመፅሃፉ አብይት ጭብጦች፥ አፃፃፍና አተራረክ ዙሪያ እንነጋገራለን። ለመፅሃፉ መነሻ ወደ ሆነው ጊዜና ቦታ ለአፍታም ቢሆን በምናብ እንጓዛለን።
በማከታተልም፥ መፅሃፉ በሚዳስሰው ትልቅ የታሪክ ጭብጥና ሥነ-ፅሁፋዊ ይዘቱ ዙሪያ ሞያዊ ሂስ የሚሰጡ የታሪክና የሥነ ፅሁፍ ባለሞያዎች እናወያያለን።
ከደራሲዋ ወ/ሮ ቆንጅት ብርሃን ጋር የነበረንን ቆይታ ቀጥሎ ያድምጡ።