በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ክርክር፥ "ባህላችን በፖለቲካችን ላይ ያለው አንድምታ"


የሃሳብ ልዩነቶቻችን እንዳሉ ሆነው ፍሬያማ ክርክር ማድረግ እንችላለን። በተለያዩ ሃሳቦች ባለቤትነታችን ብቻ በባላጋራነት ልንተያይ አይገባም። የክርክሩ ተሳታፊዎች በጋራ የሚስማሙበት ብቸኛ ነጥብ።

«ባህላችን የሁለንተናዊ ማንነታችን መሠረት ነውና እሱን ይዘን እንከኖቹን ነቅሰን ማሻሻልና ማጎትበት እንችላለን፤» የሚለውን መከራከሪያ የያዘ ተከራካሪ በአንድ ወገን «የለም ባህላችን፤ ይልቁንም ደግሞ የፖለቲካ ባህላችን መሠረታዊ ለውጥ ይሻል፤ ዛሬ ላሉን ችግሮችም የአንዳንዱ መነሻ ነውና ከሥር መሠረቱ መቀየር አለበት፤» የሚለውን የያዘው ደግሞ በሌላው ተሰልፈዋል።

የክርክሩ ተሳታፊዎች የቶሮንቶ ካናዳ ነዋሪዎቹ ዳንኤል ጥላሁንና ኪሩቤል ፍሬው ናቸው። በቅርቡ ባቋቋሙት «አድባር የክርክር መድረክ፤» በተሰኘው ማኅበራቸው ከተሟገቱባቸው ርዕሶች አንዱ የሆነው ይኸ የመከራከሪያ ነጥብ ነው በሦሥት ተከታታይ ክፍሎች የተካሄደው ክርክር መንደርደሪያ።

የክርክሩን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤

ሁለተኛውን ክፍል ክርክር ከዚህ ያድምጡ፤

የክርክሩን የመጨረሻ ክፍል ደግሞ ቀጥሎ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG