በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ ቀንድ ለምግብ ዕጥረት የተጋለጡ ከሚልዮን በላይ ህፃናት የሞት አደጋ እንዳዣበበባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ


የአፍሪካ ቀንድ
የአፍሪካ ቀንድ

በአፍሪቃ ቀንድ ግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ ሕፃናት ከተመጣጠነ ምግብ እጦት ጋር በተያያዘ ለማይቀር የሞት አደጋ ተጋልጠዋል፤ ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF ሪፖርት አደረገ። ድርጅቱ፥ ሌሎች ተጨማሪ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ ሕፃናትም ተመሳሳይ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል።

አሁን በቅርቡ ከኢትዮጵያና ኬንያ የተመለሱ ሁለት ከፍተኛ የዓለሙ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኰሚሽን ባለሥልጣናትም፥ ሁኔታው በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የድርቅ ሰለባዎች በተለይ በሕፃናቱ ላይ የበረታ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የዘገባውን ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG