በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ዛሬም በሴቶች ግርዛት የሚያምኑ አያሌ ናቸው


ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የሚፈረጀው የሴቶች ግርዛት የሚያስከትላቸውን አስከፊ ጉዳቶች ለማስቀረት ታለመው የተከናወኑ ሥራዎች ሁነኛ ለውጥ ማስመዝገብ ቢያስችሉም፤ የተለያዩ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች በወለዷቸው እምነቶች ሳቢያ ግን ቁጥራቸው የበዙ ሴቶች ዛሬም ግርዛት ይፈፀምባቸዋል።

ይህን መሰሉ በሥፋት የታመነበት፥ አደገኝነቱና በሴቶች ላይ በዘለቄታው የሚያስከትላቸው ጉዳቶች በጉልህ የታወቀ ምግባር ለጨቅላ ልጆቻቸው በሚሳሱና መልካም የሚመኙ ወላጆች እንዴት ይፈፀማል? በታላላቅ ከተሞች ሳይቀር ብዙዎች እንደምን ይህን ከመሰሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መራቅ ተሳናቸው?

ውጤታቸው ጎጂ፥ መነሻ መሠረታቸው የተሳሳተ እሳቤም ቢሆን፤ ማኅበረሰቦች በልማድ ለረዥም ጊዜ ሲያከናውኑ የቆዩትን ድርጊት ለማስተውስ የትኞቹ መንገዶች ሰርተው ይሆን?

ለእነኚህና ሌሎች ተዛማች ጥያቄዎች፥ በርዕሱ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ በሚንቀሳቀሱ ለትርፍ ያልቆሙ ድርጅቶች አማካኝነት አዲስ አበባ ውስጥ በእንግሊዝኛ የሚታተም መፅሄት ዋና አዘጋጅ ከሆነች ወጣት ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG