በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታላቁ ማክሰኞ ምርጫና የፉክክሩ ሜዳ


ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩነት በሚደረገው ትንቅንቅ አንድ ትልቅ ምዕራፍ በትላንቱ “ታላቁ ማክሰኞ፤” ተዘጋ።

Super Tuesday በመባል በሚታወቀው በዚህ በ10 ግዛቶች በአንድ ቀን የሚካሄድ የምርጫ ውድድር የትላንቱ የሪፐብሊካን ፉክክር ለቀድሞው የማሳቹሴትስ ክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ የቀዳሚነቱን መንበር ያጎናጽፍ እንጂ፤ መጪውን ውድድሮች፥ ይልቁንም በመጨረሻው የፓርቲው ዕጩ ሆኖ የሚቀርበውን ተወዳዳሪ ጠንካራ ሆኖ እንዲወጣ የማያስችል መሆኑ ተዘግቧል።

በምርጫው ሂደት፥ ውጤቶችና በመጪው የውድድሩ ገጽታዎች ዙሪያ ሞያዊ ትንታኔ የሚሰጡን የፖለቲካ ምሁር ጋብዘናል።

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም ሳንበርናንዲኖ በሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የህግ ባለ ሞያ ናቸው።

የትንታኔውን ሙሉ ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG