በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጅቡቲው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት አስቀድሞ የተወሰነ ነው ተባለ


የጅቡቲ መንግስት በስድስት ሰዓታት ውስጥ የምርጫ ካርዶችን ቆጥሮ የመጨረሻውን ውጤት አሳውቃለሁ ማለቱ የምርጫውን ውጤት ቀድሞውኑ የታወቀ ያደርገዋል።

የፕሬዝዳንት ኦማር ጌሌን መንግስት በመቃወም አደባባይ የወጡ ጅቡቲያውያን በመንግስቱ ወታደሮች በኃይል እንዲበተኑ ከተደረጉበትና ታዋቂ የተቃዋሚ መሪዎችን ጨምሮ በርካቶች ለእስር ከተዳረጉበት ያለፈው የካቲት 11 አንስቶ ኅዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ባያቋጡም፤ የዜጎች በነፃ የመሰብሰብና የመቃወም መብት አሁንም እንደተገደበ ነው።

”ተቃዋሚዎች እየተዋከቡና የመንግስቱ የኃይል መዳፍ እያረፈባቸው ባሉበት፤” ምርጫው ነፃና ሚዛናዊ ይሆናል፤ ብሎ እንደማያምን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት Human Rights Watch አስታውቋል።

ምርጫው በሚካሄድበት በዛሬው ዕለት በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች በሰዓታት ውስጥ በፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ከተፈቀደላቸው ኅዝባዊ እንቅስቃሴ መበተናቸውም ተዘግቧል።

የምርጫውን ሂደትና የሚጠበቀውን ውጤት አስመልክቶ ለተጠናቀረው አጭር ዘገባ ዝርዝር ተከታዩን ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG