በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መፍትሄ አምጪ ሃሳቦች በዋይት ሃውስ ለለውጥ ሃዋሪያነት አበቁ


«አሥራ አራቱም ግለሰቦች የተሰማሩበት አቅጣጫ ቢለያይም፤ በመሠረቱ አንድ ሆኖ ያገኘሁት፤ ዜጎች፥ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ በአካባቢያቸው ላለው ችግር መፍትሄ ለማምጣት ራሳቸው መንቀሳቀስ እንደሚችሉና ያንን ደግሞ በአረዓያነት ለማሳየት “ይቺን የራሴን መሥራት እችላለሁ፤” ብለው መነሳታቸው በሁሉም ላይ በጋራ ያየሁት የዝግጅቱ ነፀብራቅ ነበር።» አቶ ጥበቡ አሰፋ ከሰሞኑ የዋይት ሃውስ የለውጥ ሃዋርያ ዕውቅና ተሸላሚዎች አንዱ።

ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ White House እና የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በትብብር በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት፥ ለማኅበረሰብ ዕድገትና የሰመረ ህይወት በታለሙ ሥራዎቻቸው የተመረጡ 14 የምሥራቅ ተወላጅነት ያላቸው አሜሪካውያን የአክብሮት እውቅና ተሸለሙ።

«መፍትሄ አፍላቂ፤» ሃሳቦች የሚል ቁልምጫ ከተሰጣቸው ከእነኚህ ተሸላሚዎች ሥራ ያንዱን መነሻ ያደረገ ቃለ ምልልስ የባህልና ማኅበረሰብ ቅንብር ይዞ ቀርቧል።

የቃለ ምልልሱን የመጀመሪያ ክፍል ለማድመጥ ቀጥሎ ያለውን ይጫኑ።የቃለ ምልልሱን ሁለተኛ ክፍል ለማድመጥ ቀጥሎ ያለውን ይጫኑ።

የቃለ ምልልሱን አጠር ያለ የመጨረሻ ክፍል ለማድመጥ ቀጥሎ ያለውን ይጫኑ።


XS
SM
MD
LG