በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት: «ቡና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፥ ባህልና ልማት!» የመጀመሪያ ክፍል፤


በቦስተን ዩኒቨርሲቲ የፍሬዴሪክ ፓርዲ የጥናት ማዕከል ለህትመት የበቃውና የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና የንግድ ምልክት ባለቤትነት ያረጋገጠውን ጥረት በምሳሌነት የተመለከተው ይህ ጥናት፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነትን የሚያስጠብቀው ኅግ እስካሁን እምብዛም ተጠቃሚ ያላደረጋቸውን ባለ አነስተኛ ገቢ አገሮች፤ እንደ ግዙፉ አትራፊ ኩባንያዎች ሁሉ፥ የትሩፋቱ ተቋዳሽ ሊያደርግ የሚያስችል አቅም እንደሚያጎናፅፍ ያመላክታል።

አንድ የምርት ውጤት በቁሳዊ ይዘቱ ከሚያስገኛቸው ቀጥተኛ ጠቀሜታዎች ባሻገር፤ ከምርቱን ልዩ መሆን፥ ምንነት፥ ሥምና ዝናው ወይም ዕውቅናና፤ እንዲሁም ምርቱ የፈለቀበትን ባህል በመሳሰሉ ባህሪያቱ አማካኝነት የሚያስገኛቸው ዋነኞቹ ከአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ዕሴቶች ናቸው።

«ቡና፥ ባህልና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፤» በሚል ርዕስ ከተሰናዳው ተከታታይ ውይይት፤ የታሪክ አጥኚዋ ዶ/ር ሄራን ሰረቀብርሃን በጥናታቸው በመረመሯቸው ጭብጦች ዙሪያ፤ የደሃውን የቡና አምራች ገበሬ ከምርት ፍሬው ተጠቃሚ እንዲሆን ይሆን ዘንድ በተነጣጠሩ ፅሁፎቻቸው ከታወቁትና የዓለም አቀፉ ቡና መጠጪያ ሱቆች ባለቤት ዕውቁ የStarbucks ኩባንያ ዋና መቀመጫ የሆነችው የዩናይትድ ስቴትሷ ሲያትል ከተማ ነዋሪ አቶ ወንድወሰን መዝለቂያ ይወያያሉ።

የውይይቱን አጠር ያለ የመጀመሪያ ክፍል እነሆ!

XS
SM
MD
LG