በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ፥ ድህረ ሙባረክ፤ ወደ የት ታመራ ይሆን?


በግብፅ የተካሄደው የወጣቶች አብዮት፥ ለሰላሳ ዓመታት በጠንካራ መዳፍ አገሪቱን የገዙትን ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክን የማይነቃነቅ ይመስል ከነበረ መንበራቸው አወረደ።

በታህሪር አደባባይ ከትሞ ለአስራ ስምንት ቀናት ጎልቶ ሲሰማ የቆየው ኅዝባዊ የተቃውሞ ድምፅ ዛሬ አሸናፊነቱን አረጋገጠ።
ከሁለት ሳምንታት በላይ ለሆነ ጊዜ ያለማቋረጥ በየቀኑ አደባባይ እየወጣ ፕሬዝዳንቱ ስልጣናቸውን ይለቁ ዘንድ ሲጠይቅ የሰነበተው የኅዝብ የቁጣ ድምፅ በመጨረሻው በሙባረክ ከስልጣን መውረድ ቢጠናቀቅም፤ የአገሪቱን ቀጣይ ዕጣ አስመልክቶ ግን በርካታ ጥያቄዎችን ተነሱ እንጂ አልተመለሱም።

«ግብፅ፤ ከሙባረክ ስንብት በኋላ ዕጣዋ ምን ይሆን? ወደ የትስ እያቀናች ነው? ማን፥ ምን ዓይነት ሚና ይኖረዋል?» የሚሉትንና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለመፈተሽ ተንታኞች ጋብዘናል።

ውይይቱን እነሆ፤

XS
SM
MD
LG