በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳ ለአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበርነት ተመረጡ


አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ባካሄደዉ ሁለተኛዉ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳን በሊቀመንበርነት መረጠ። ዶክተር ነጋሦ ከዶክተር ንጋት አስፋዉና ከአቶ ዘለቀ ረዲ ጋር ተወዳድረዉ በ197 ድምጽ ብልጫ እንዳሸነፉ በፓርቲዉ ጉባኤ ላይ ተገልጿል።

ዶክተር ነጋሦ ጊዳዳ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ ባሁዋላ ባደረጉት አጭር ንግግር፣ ድርጅታቸዉ ላይ የተጋረጡ ያሏቸውን አበይት ነጥቦች አንስተዋል። አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በአደረጃጀት፣ በሰዉ ኃይልና በገንዘብ ደካማ መሆኑን ጠቁመዉ እንዲጠናከርም ተግተዉ ለመሥራት ቃል ገብተዋል።

መንግስት የፓርቲያቸዉ አመራር አባላት የሆኑ ንጹሐን ዜጎችን በአሸባሪነት ሽፋን ወንጅሎ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እያደረገ ነው፤ ያሉትን ሩጫ እንደሚቃወሙ ገልጸዉ፤ ያሠራቸዉን የአመራር አባላት በፍጥነት እንዲፈታ ጠይቀዋል።

ኢህአዴግ የፖለቲካ ምህዳሩን መቆጣጠሩን ከቀጠለና በአገሪቱ ፓለቲካ ተቃዋሚዎችን ካላሳተፈ ሕዝቡ መብቱን ለማስከበር መነሳቱ አይቀርም ብለዋል ዶክተር ነጋሦ። ፓርቲያቸዉ አንድነት ከሌሎች «ሃቀኛ፤» ተቃዋሚ ከሚላቸዉ ድርጅቶች ጋር ያከናዉናቸዉ ተግባራት አኩሪ መሆናቸዉን ተናግረዉ፣ በፖለቲካ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች መፍትሔ ዙሪያ ከእነዚህ ድርጅቶች ጋር መሥራት እንደሚቀጥል ቃል አመልክተዋል።

የዘገባውን ሙሉ ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG