በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ የዛሬ ይዞታውና አካሄዱ፤ ከየት ወደ የት?


«የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፤ ወቅታዊ ይዞታና አንድምታው፤» በእሰጥ አገባ የተጀመረው የሁለት ወገን ክርክር ቀጥሏል።

የክርክሩ ተሳታፊዎች፥ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ከአዲስ አበባ፤ አቶ ግዛው ለገሰ ደግሞ ከዚህ ከዋሽንግተን ዲሲ ናቸው። አቶ ተስፋዬ ”የንግር ነፃነት“ ዛሬ በኢትዮጵያ «ተረጋግጧል፤» ሲሉ፤ አቶ ግዛው በበኩላቸው፤ ከዓመታት በፊት ብልጭ ብሎ የነበረውና እንዲያድግ፥ እንዲጎለብት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ዛሬ ጨርሶ ተዳፍኗል፤ ይላሉ።

የንግግር ነፃነት በኢትዮጵያ፥ ከማጡ ወደ ድጡ? ወይስ በእርግጥ «ሁነኛ፤» የሚሰኝ ነፃነት ዕውን እየሆነ ይሆን? የማይመሳሰሉና ፍፁም የተለያዩ ዕይታዎች የተንፀባረቁበት የሁለት ወገን ክርክር እንደጦፈ ቀጥሏል።

ለዝርዝሩ የሳምንቱን ምጥን ዝግጅት ያዳምጡ፤

XS
SM
MD
LG