በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥብቅና፥ የውጭ አገር ዜግነት ላላቸው የኢትዮጵያ ተወላጆች ከማይፈቀዱ የሥራ መስኮች አንዱ


«መንግስት የገባውን ውል አፈረሰ፤» ይላል የፅሁፋቸው ርዕስ። የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው የኢትዮጵያ ተወላጆች በአገር ውስጥ «ሊሰማሩበት አይችሉም፤» መባሉ አነጋጋሪ የሆነበትን አንድ የሥራ መስክ ይመለከታል።

ሙልጌታ አረጋዊ አረጋዊ ይባላሉ። ቀደም ሲል በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በጥብቅና ሞያ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱበት ካለፈው ዓመት አንስቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የኅገ-መንግስት እና የመገናኛ ብዙኃን ህግ ትምህርቶች መምህር ናቸው።

በሌሎች የተለያዩ የሥራ መስኮች ዙሪያ የሚነሱ መሰል ጥያቄዎችም በተለያዩ ጊዜያት ይሰማሉ። አቶ ሙልጌታ አዲስ አበባ ውስጥ በሚታተም አንድ የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ለንባብ ያበቁትን ፅሁፍ መነሻ ያደረገ ቃለ ምልልስ በተለይ በጥብቅና ሞያ ላይ ያተኩራል።

የመጀመሪያውን ክፍል ቃለ ምልልስ ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG