በኮርያ ዘመቻ ከዓለም አቀፉ የጥምረት ኃይል ጎን ለተሰለፉ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ክብር የተሰናዳ ሥነ ሥርዓት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ተካሄደ።
ለኢትዮጵያውያኑ የኮርያ ዘማቾች ክብር የተሰናዳው ሥነ ሥርዓት የተከናወነው፥ በትላንትናው ዕለት በተካሄደው 60ኛው የኮርያ ጦርነት አርበኞች መታሰቢያ በዓል ላይ ነው።
የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስቴር ከተለያዩ ክፍሎች ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ ሥነ ሥርዓት ክብሩን የተጎናጸፉ ሁለት ኢትዮጵያውያን የኮርያ ዘማች አርበኞች፤ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ተወካዮች፥ የኢትዮጵያና የኮርያ ሪፐብሊክ ተጠሪዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዋሽንግተን ዲሲው የኮርያ ዘመቻ አርበኞች መታሰቢያ ሃውልት አቅራቢያ የተከናወነውን ይህንን ሥነ ሥርዓት አሉላ ከበደ ተከታትሎታል።