በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥብቅና፥ የውጭ አገር ዜግነት ላላቸው የኢትዮጵያ ተወላጆች ከማይፈቀዱ የሥራ መስኮች አንዱ


«መንግስት የገባውን ውል አፈረሰ፤» የሚለውን ፅሁፋቸውን ተንተርሶ ከአቶ ሙልጌታ አረጋዊ ጋር የጀመርነው ቃለ ምልልስ ሁለተኛ ክፍል የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው የኢትዮጵያ ተወላጆች በአገር ውስጥ «ሊሰማሩበት አይችሉም፤» መባሉ አነጋጋሪ የሆነበትን የሥራ መስክ ይመለከታል።

የመንግስት ሥልጣን ገደብ፥ ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድንጋጌዎችና የሌላ አገር ዜግነት ያላቸው የኢትዮጵያ ተወላጆች በትውልድ አገራቸው በተለያዩ ሥራዎች የመሥራት ፍላጎትና የተከለከሉ ወይም ያልተፈቀዱ ሥራዎች፤ በቃለ ምልልሱ ከሚጎበኙ ነጥቦች ውስጥ ናቸው።

አቶ ሙልጌታ ቀደም ሲል በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በጥብቅና ሞያ ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱበት ካለፈው ዓመት አንስቶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የኅገ-መንግስት እና የመገናኛ ብዙኃን ህግ ትምህርቶች መምህር ናቸው።

የቃለ ምልልሱን ሁለተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG