በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለረዥም ጊዜ ከአዕምሮ አልወጣ ብሎ የሚያስቸግር ሃሳብ የሚያስከትለው የበሽታ ዓይነት


ለሰዓታት ከአዕምሮ አልወጣ ብሎ የሚያስቸግርና አንዳች ነገር ደጋግመው እንዲያደርጉ የሚገፋፋ ሃሳብ እንደምን የዕለት ኑሮን ማከናወን እስኪያዳግት ድረስ ይዘልቃል? ለመሆኑ እንዲህ ያለው በሽታ ምንድነው? ከምን ይመጣል? እንዴትና በምንስ ይረዳል?

በደቡብ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት የዴንቨር ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ አድማጫችን ያደረሱንን ጥያቄ መሠረት ያደረገው የምሽቱ የሃኪምዎን ይጠይቁ ቅንብር የመጀመሪያ ክፍል ይመለከታተዋል።

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሚሰጡን በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ታዋቂው የሜዮ ክሊኒክ የኒውሮሎጂና የሳይካትሪ ማለትም የነርቭና የስነ አዕምሮ ህክምና ትምህርቶች ተባባሪ ፕሮፌሰርና የህክምና ክፍሉ ዲሬክተር ናቸው።

ለዝርዝሩ ቅንብሩን ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG