በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ከዩናይትድ ስቴይትስ ጋር የጠበቀ የንግድ ግንኙነት እንጂኖራት ፕሬዝደንት ሁ ጥሪ አቀረቡ


ባራክ ኦባማ (ግራ) የቻይናው ፕሬዝዳንት ሁ ጂንታው በዋሽንግተን ተገናኝተው ሲነጋገሩ
ባራክ ኦባማ (ግራ) የቻይናው ፕሬዝዳንት ሁ ጂንታው በዋሽንግተን ተገናኝተው ሲነጋገሩ

የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ጂንታው በዩናይትድ ስቴይትስ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ1989ወዲህ በዩናይትድ ስቴይትስ መንግስታዊ ልዑካንን በመምራት የቻይና ፕሬዝደንት ወደ ዩናይትድ ስቴይትስ ሲጓዝ ሁ የመጀመሪያው ናቸው።

በዚህ ጉብኝታቸው ሚስተር ሁ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአንድሩውስ ወታደራዊ የአውሮፕላን ማረፊያ በምክትል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ ዛሬ በዋይት ሀውስ ቤተ-መንግስት ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

የአሜሪካ ኩባንያዎችና ድርጅቶች ዋጋው ከወረደው የቻይና ገንዘብ ጋር በዶላር ለገበያ ውድድር መቅረብ ከብዶናል በሚል ሮሮ ማሰማት ከጀመሩ ቆይተዋል። በይፋ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስትና የመገናኛ ብዙሃን ችግሩን አስመልክቶ መላ መምታት ከጀመሩ አንድ አመት አልፎታል። እስካሁን የተለወጠ ነገር የለም።

የቻይናው ፕሬዝደንት ሁ ከዩናይትድ ስቴይትሱ አቻቸው ባራክ ኦባማ ጋር በንግድ ዙርያ ሲመክሩ ሰንብተዋል። በሰፊው ውይይት ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቀው ጉዳይ ቻይና የሀገር በቀል ድርጅቶቿን ታበረታታለች ለውጭ ሀገር ኩባንያዎች ገበያ በተለያዩ የቢሮክራሲና የህግ ማነቆዎች ገበያ እንዳያገኙ ትጥራለች በሚል አሜሪካዊያን ነጋዴዎች ያማርራሉ።

በተለይ ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በማደግ ላይ ያለውን ያቻይናን ኢንዱስትሪ የገበያቸው መዳረሻ ለማድረግ ይፈልጋሉ፤ ግን ማነቆዎቹ በዝተውባቸዋል።

ሚስተር ኦባማ ያቻይናንና አሜሪካን የትምህርት፣ የቴክኖሎጂ፣ የንግድና የቱሪዝም ግንኙነት መጠናከር አስመልክተው፤ በብዙዎቹ መስኮች ተወዳዳሪዎች ብንሆንም በብዙዎቹ ደግሞ አብረም መስራት እንችላለን ብለዋል።

ሚስተር ሁ ጂንታውም በበኩላቸው ወደ ዩናይትድስቴይትስ የመጡት የሁለቱን አገሮችና ህዝቦች ትብብር፣ አጋርነት፤ እንዲሁም እርስ-በርስ መተማመን ለማጠናከር መሆኑን ተናግረዋል። ሚስተር ሁ ይሄ ግንኙነት በጸና መሰረት ላይ መቆም ያለበት መሆኑን ገልጸዋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG