በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጸረ-ሽብር ህጎች አተገባበርና በንግግር ነጻነት ላይ የሚያሳድሩት አሳሳቢ ተፅዕኖ


«የትኛውም መንግስት የሽብር አደጋዎችን የመከላከል ግዴታ እንዳበት ግልጽ ነው። ሆኖም የጸረ-ሽብር ህጎች አተገባበር አንዳንዴ የንግግርና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን መሸርሸር መቻሉን አስመልክቶ ያደረብንን ሥጋት ገልጬላቸዋለሁ።» የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር William Burns

በቅርቡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪቃ አገሮች ያደረጉትን የአንድ ሳምንት የሥራ ጉብኝት አጠናቀው የተመለሱት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር William Burns በጉብኝታቸው ወቅት በቁልፍ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ከአህጉሪቱ መሪዎችና የማኅበረሰብ ተጠሪዎች ጋር መነጋገራቸውን ጠቁመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር Hilary Clinton በቅርቡ በምዕራብ አፍሪቃ ያደረጉትን የሥራ ጉብኝት የተከተለው ጉብኝታቸው የፕሬዝዳንት ኦባማ አስተዳደር ለአፍሪካ የሚሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያመላክት መሆኑን የተናገሩት Mr Burns አገራቸው ከአፍሪቃ ጋር በምታደርገው ትብብር አህጉሪቱ ያሏትን ዕድሎች ለማሳደግና «የጋራ ፈተናዎቻችን፤» ባሏቸው ጉዳዮችም ላይ የያዙትን ያልተቋረጠ ትኩረት እንደሚያጠናክር አስረድተዋል።

ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ከጉብኝታቸው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያን የጸረሽብር ህግ አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፥ በጉዳዩ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚንስትር መለስ ጋር በነበራቸው ቆይታ አንስተው መነጋገራቸውን አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG