በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን ጣቢያ - ኢሳት፤ ለኢትዮጵያ መንግሥት የሥርጭት ማፈኛ ቴክኖሎጂና ሥልጠና እየሰጠች ነው፤ ያላትን ቻይናን ወነጀለ


ለሁለት ወራት ተስተጓጉሎ የቆየው የ«ኢሳት፤» ማለትም የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት ከጀመረ በኋላ እንደገና በማግሥቱ መቋረጡ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በአምስተርዳም፥ ዋሺንግተን ዲ ሲ እና ለንደን እንዳሉት ከሚገልጻቸው ስቱዲዮዎቹ ሥርጭቱን ማስተላለፍ የጀመረው እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከሚያዝያ 2010ዓም ጀምሮ ሲሆን በተደጋጋሚ ችግሮች ገጥመውታል። ለነዚህ ችግሮቹ በዋናነት የሚጠቅሰውም፥ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ መንግሥት ይሰጣል ያለውን የሥርጭት ማፈኛ ቴክኖሎጂና የሥልጠና እርዳታ ነው።

ኢሳት ይህንኑ አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ መነሻ በማድረግ የተጠናቀረውን የዚህን ዘገባ ዝርዝር ቀጥሎ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG