ዋሺንግተን ዲሲ —
ዙማ ከፈረንሳይ የጦር መሳሪያ አምራች ኩባኒያ ጉቦ ተቀብለዋል ተብለው ተከሰዋል። ቴልስ እኤአ በ1999 በሳቸው ዘመነ መንግሥት ከደቡብ አፍርካ ጋር የሁለት ቢሊዮን ዶላር መሳሪያ ግዢ ውል ተፈራርሟል። ዙማ በጥቅሉ አሥራ ስድስት የማጭበርበር የመንግሥት ገንዘብ ሥርቆት እና አስገድዶ ወንጀል ማስፈጸምን ጨምሮ ክሶች ተመስርቶባቸዋል።
“ዙማ ታመወል የውጭ ሃገር ህክምና ፍለጋ ላይ ናቸው” ያሉት ጠበቆቻቸው የዙማ ጠበቆች በጦር ኃይሎች ሃኪም የተፈረመ ያሉትን ደብዳቤ አቅርበዋል። ይሁን እንጂ ዳኛው የእስር ማዘዣው ለግንቦት ወር እስከተሰጣቸው ቀጣይ ቀጠሮ እንዲፀና አዘዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ