ዋሽንግተን ዲሲ —
በዓለም 5ቱ ኃያላን አገራት የኒዩክሊየር ጦር መሣሪያ የበለጠ እንዳይስፋፋ ለመግታት ሊደርስ የሚችለውን የኒዩክሊየር ግጭት ለመለካከል በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ትናንት ሰኞ ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታወቁ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላት የሆኑት በቡድን ስማቸው P5. የሚባሉት አምስቱ አገራት ቻይና፣ ፈረንሳይ፣ ሩሲያ፣ እንግሊዝና ዩናይትድ ስቴትስ ባወጡት መግለጫቸው “እንደዚያ ያሉ የጦር መሳሪያዎች መሰራጨት የሌለባቸው መሆኑን አበክረን እናምናለን” ብለዋል፡፡
አገሮቹ ጨምረውም “የኒዪክሊየር ጦርነት የሚያሸንፉት ባለመሆኑ ጦርነቱም መቸውም ቢሆን መካሄድ የሌለበት መሆኑን እናረጋግጣለን” በማለት ስምምነታቸው አስረግጠው ተናገረዋል፡፡
ስምምነቱ የመጣው ከኃያላን አገራት ጋር የተደረገውን የኢራን ኒዪከለየር ስምምነት የሚከልሰው ስብሰባ ትናንት ሰኞ በተደረገበት ወቅት ነው፡፡