በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡሩንዲ የታጠቁ ሰዎች በተመድ ከፍተኛው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ቢሮ ላይ ጥቃት አደረሱ

ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ዛሬ ረቡዕ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ቢሮ ቅፅር ግቢ ጥሰው ገብተው ጥቃት ማድረሳቸው ተገለጠ።

ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ዛሬ ረቡዕ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ቢሮ ቅፅር ግቢ ጥሰው ገብተው ጥቃት ማድረሳቸው ተገለጠ።

ይህ የሆነው የኮሚሽኑ መርማሪ አካል ቡሩንዲ ውስጥ ያለፍርድ ሂደት መግደል፣ ማሰር እና ማሰቃየት እና ወሲባዊ ጥቃት ጨምሮ በሰብዕና ላይ ወንጀል ሳይፈፀም እንዳልቀረ የሚገልፁ ሪፖርት ካቀረበ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነው።

ቡሩንዲ ፕሬዚዳንቷ ፒየር ኑኩሩዚዛ ከሁለት ዓመታት በፊት አወዛጋቢ በሆነ መንገድ ሶስተኛ የስልጣን ዘመን ካሸነፉበት ጊዜ ወዲህ በፖለቲካ ሁከት እየታመሰች ናት።

የመንግሥታትቱ ድርጅትት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ቢሮ ላይ በተፈፀመው ጥቃት በሰውና ንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት ለጊዜው የተሰጠ መረጃ የለም።

የቪኦኤ የማዕከላዊ አፍሪካ ዘጋቢ እንዳለው ታጣቂዎቹ የተመዱ ቅፅር ግቢ ጥሰው የገቡት የግቢውን የጥበቃ ኃይሎች ካንበረከኩ በኋላ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG