አንድ ከኢንዲያና ግዛት አካባቢ እንደመጣ የተገመተ እና በዋይት ሐውስ አካባቢ መሳሪያ ታጥቆ፣ ከፖሊስ ጋራ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቷል የተባለ ግለሰብ ፣ “ሴክሬት ሰርቪስ” በመባል በሚታወቀው፣ ዩናይትድ ስቴትስ የፕሬዝደንታዊ የደኅንነት ጥበቃ አባላት መመታቱን ባለሥልጣናት አስታወቁ።
ከዋይት ሐውስ በአንድ አካፋይ መንገድ ብቻ በሚርቅ ቦታ ላይ፣ እኩለ ሌሊት አካባቢ በተፈጠረው በዚኽ ክስተት ከታጠቀው ገለሰብ በስተቀር የተጎዳ ሌላ ሰው አለመኖሩን የ"ሴክሬት ሰርቪሱ" መግለጫ አመልክቷል። በሰዓቱም ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ፍሎሪዳ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነበሩ ተብሏል።
የጥበቃ አገልግሎቱ፣ "አንድ ራሱን ሊያጠፋ ነው" በሚል የሚጠረጠር ግለሰብ ከኢንዲያና ተጉዞ መምጣቱን ከአካባቢ ፖሊስ መረጃ እንደደረሰው ገልጾ፣ ከተሰጠው ዝርዝር መግለጫ ጋራ የሚመሳሰለውን መኪና እና ግለሰቡን በዋይት ሐውስ አቅራቢያ ማግኘቱን አስታውቋል።
"ፖሊስ ወደ መኪናው እየቀረበ ሲኼድ ግለሰቡ መሳሪያ በማውጣት እሰጥ አገባ ገጠመ፣ በዚኽ ወቅትም ከኛ በኩል ርምጃ ተወስዷል" ሲል ፕሬዝደንታዊ ደኅንነት ጥበቃ አገልግሎቱ በመግለጫው ላይ አስፍሯል።
ግለሰቡ ሆስፒታል እንደሚገኝ የጠቆመው መግልጫው ፣ አኹን ያለበት ኹኔታ ግን "አይታወቅም" ብሏል።
መድረክ / ፎረም