በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አምነስቲ በኒጀር ህጻናት እየተገደሉ ለጦርነት እየተመለመሉ ነው አለ


ፎቶ ፋይል፦ የተማሪ ወላጆች ኒጀር ውስጥ በሚገኘው ሳሊሁ ታንኮ ት/ቤት በመገኘት በመወያየት ላይ
ፎቶ ፋይል፦ የተማሪ ወላጆች ኒጀር ውስጥ በሚገኘው ሳሊሁ ታንኮ ት/ቤት በመገኘት በመወያየት ላይ

የኒጀር አዋሳኝ በሆኑ የማሊና ቡርኪናፋሶ ድንበር አካባቢ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ ህጻናት እየተገደሉ ወይም ለውትድርና እየተመለመሉ መሆኑን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ ባወጣው ጥናታዊ ሪፖርት አስታወቀ፡፡

ሪፖርቱ “ቲላቤሪ በተባለው የኒጀር ግዛት ጠቅላላ ትውልድ እንዳለ በሞትና በጥፋት የተከበበ ነው” ብሏል፡፡

አምነሰቲ በዚህ በ2021 ብቻ 60 ህጻናት መገደላቸውን ባለ 51 ገጽ በሆነው ሪፓርቱ አመልክቷል፡፡ ካለፈው ዓመት ወዲህ በተካሄዱ ግጭቶች ብቻ 544 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውንም አስታውቋል፡፡

የአምነስቲ የቀውስ ምላሽ ምክትል ድሬክተር ማት ዌልስም “ታጣቂ ቡድኖች ትምህር ቤቶችና የመጠባበቂያ ክምችት ስፍራዎችን በተከታታያ እያጠቁ ህጻናትን ለምልመላ ኢላማ እያደረጉ ነው፡” ብለዋል፡፡

አምነስቲ ለዚህ ተጠያቂ ያደረጋቸው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱትን የታላቁ ሰሃራ አይሲስ እና እንዲሁም ከአልኬዳ ጋር ግኙነት አላቸው የተባሉትን ጃማት ነርሳት አል ኢስላም ዋል ሙስልሚ የተባሉትን ድርጅቶች ነው፡፡

XS
SM
MD
LG