በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሕወሓት የትግራይ ሕዝብን አይወክልም" - አረና ትግራይ


አረና ትግራይ ቅዳሜ ዕለት በመቀሌ ያካሄደ ሰልፍ
አረና ትግራይ ቅዳሜ ዕለት በመቀሌ ያካሄደ ሰልፍ

አረና ትግራይ ቅዳሜ ዕለት በመቀሌ የጠራው ሰልፍ በፀጥታ ኃይሎች አማካኝነት የታወከ እንደነበር ገልፆ ነገር ግን በብሔር ላይ ያነጣጠር ግድያ ይቁም፣እኛ ኢትዮጵያውያን አንድ ነን፣ ሕወሓት የትግራይ ሕዝብን አይወክልም የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን የያዘ ሰልፍ መካሄዱን አስታውቋል።

"ሕወሓት ዘወትር በፕሮፖጋንዳ መልክ የሚነዛው ድርጅቱና የትግራይ ሕዝብ አንድ እንደሆኑና ላደረሰው ጉዳት የትግራይ ሕዝብን ተጠያቂ ለማድረግ በርካታ ግዜ እንዲህ ያሉ ምልክቶች ያሳያል። የዚህ የፕሮፖጋንዳ ውጤትም የተለያዩ ኃይሎችም ሆነ ቁጥሩ የማይናቅ የኢትዮጵያ ሕዝብም በአንድ ዓይነት የማየት አዝማሚያ ማየት አለ" የሚለው የአረና ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አምዶም ገብረስላሴ "ሕዝብና ድርጅት አንድ መሆን ስለማይችሉ ይህ መቆም አለበት። ሕወሓት አምባገነን እና አፋኝ ሥርዓት ነው የትግራይ ሕዝብ ግን እንደሌላው ሕዝብ ጭቁን ነው" ብሏል።

ዝርዝሩን ከተያይዘው የጽምፅ ፋይል ያድምጡ።

"ሕወሓት የትግራይ ሕዝብን አይወክልም" - አረና ትግራይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:20 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG