በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አረና በነገው ዕለት ሰልፍ ጠርቷል


በብሔር ላይ የሚደረግ ጥቃንት ለማውገዝ እንደሆነ ገልፆ ሕዝቡ ሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ጫና እየተደረገበት ነው ብሏል።

የአረና ትግራይ ፓርቲ በመላው ኢትዮጵያ የሚደረገውን ብሔር ተኮር ጥቃት ለማውገዝ በሚል በመቀሌ ከተማ በነገው ዕለት ለጠራው ሰልፍ የማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማው አስተዳደር ማስገባቱን እስካሁን ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን ገለፀ። ነገር ግን ሕጉ “ማሳወቅን” ብቻ የሚጠይቅ በመሆኑ ሰልፉ በነገው ዕለት እንደሚካሄድ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የቀበሌ ካድሬዎች በመቀሌ ዙሪያ የሚገኙ ነዋሪዎች በስብሰባው እንዳይገኙ የሚከለክል ግብረሃይል አቋቁመው ቤት ለቤት እየዞሩ በማስፈራራት ላይ መሆናቸውናን ታክሲዎችና ተሳፋሪዎች ድንገተኛ ፍተሻ እየተደረገባቸው ነው ብሏል - ፓርቲው።

የትግራይ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ምላሽ ለማግኘት ሞክረን ስልካቸው ስለማይነሳ ምላሻቸውን ለማግኘት አልቻልንም። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

አረና በነገው ዕለት ሰልፍ ጠርቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG